በናይጄሪያ ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት የኤሌክትሪክ ብስክሌት ዋጋ ቀነሰ
19:58 10.09.2025 (የተሻሻለ: 20:04 10.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት የኤሌክትሪክ ብስክሌት ዋጋ ቀነሰ
የአፍሪካ ቀዳሚ የኤሌክትሪክ ሞተሮች አምራች ድርጅት የሆነው ስፒሮ፤ የኤሌክትሪክ ብስክሌቶችን ተመጣጣኝ ለማድረግ በናይጄሪያ የሚገኙትን የኤኮን ሞዴል ብስክሌቶች የችርቻሮ ዋጋ ወደ 950 ዶላር ዝቅ እንዳደረገ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ይህ ውሳኔ ከሞተር ብስክሌቶች ጋር ሲነጻጸር ከነዳጅ እና ጥገና እስከ 40 በመቶ ለመቆጠብ ያስችላል።
"የኤሌክትሪክ ብስክሌት ባለቤት መሆን ህልም ብቻ እንዳልሆነ ብዙ ናይጄሪያውያን እንዲያውቁ እንፈልጋለን - ስማርት፣ ሊገዙት የሚችሉት ነው" ሲል ኩባንያው አፅንዖት ሰጥቷል፡፡
ለናይጄሪያ ገበያ የተዘጋጁት የኤኮን ሞዴል ብስክሌት፦
🟠 LED መብራቶች፣
🟠 ጠንካራ ፍጥነት መቆጣጠሪያ (ፍሬን)፣
🟠 የዩኤስቢ መሙያ፣
🟠 በአንድ ግዜ ቻርጅ እስከ 100 ኪ.ሜ፣
🟠 ዘመናዊ መከታተያ፣
🟠 በርቀት መቆለፍ የሚያስችል ይዘቶች ያሉት ነው፡፡
አሽከርካሪዎች ለአስቸኳይ ቅያሪዎች የስፒሮን ሰፊ የባትሪ መለዋወጫ መረብ በመጠቀም ግዜያቸውን መቆጠብ የሚያስችላቸው አሠራር መኖሩንም ተቋሙ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X