እስራኤል በዶሃ የፈፀመችው ጥቃት የዓለም አቀፍ ሕግንና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥስ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእስራኤል በዶሃ የፈፀመችው ጥቃት የዓለም አቀፍ ሕግንና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥስ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
እስራኤል በዶሃ የፈፀመችው ጥቃት የዓለም አቀፍ ሕግንና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥስ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.09.2025
ሰብስክራይብ

እስራኤል በዶሃ የፈፀመችው ጥቃት የዓለም አቀፍ ሕግንና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥስ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኳታር በሃማስ እና በእስራኤል መካከል በሚደረጉ ንግግሮች ላይ ቁልፍ የአሸማጋይነት ሚና እንዳላት ያነሳው ሚኒስቴሩ፤ ጥቃቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለማግኘት የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ለማዳከም ያለመ ነው ብሏል፡፡

"ሩሲያ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም በተቻለ ፍጥነት እንዲታወጅ እና የፍልስጤምን ጉዳይ በሚታወቁ የዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ከመፍታት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ መሠረታዊ እና ፅኑ አቋሟን ታረጋግጣለች" ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስረግጧል።

ሞስኮ ሁሉም አካላት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲከተሉ በድጋሚ ጥሪ አቅርባለች።

የእስራኤል ጦር በዶሃ የሃማስ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ማክሰኞ ዕለት መፈፀሙ የሚታወስ ነው።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0