- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

አፍሪካ እና ካሪቢያን፡ ለፍትህ እና ለለውጥ የተደረገ ትብብር

አፍሪካ እና ካሪቢያን፡ ለፍትህ እና ለለውጥ የተደረገ ትብብር
ሰብስክራይብ
“በካሪቢያን የሚገኙት እነዚህ ወንድሞቻችን ላለፉት 400 ዓመታት ከእናታቸው አህጉር ተነጥለው ቆይተዋል። አሁን አብረን ተገናኝተን ወደፊት ማቀዳችን፣ ስለ ካሳ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካንና የካሪቢያንን ህዝቦች፣ በተለይም ከአፍሪካ አህጉር ውጭ የሚኖሩ የአፍሪካ ተወላጆችን ህይወት ለማሻሻል ለወደፊት የጋራ እርምጃ ማቀድም ጭምር ተገቢ ነው።” አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
“በመሰረትንው ግንኙነት ወሳኙ ነገር መተባበር ነው። እኛ አንድ ህዝቦች ነን። በካሪቢያን ክልል የምንገኝ እና በአፍሪካ አህጉር የምንገኝ ሁላችንም አንድ መሆን እንዳለብን እንገነዘባለን።” ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የ2ኛው የአፍሪካ-ካሪኮም ጉባኤ ይዘት እንቃኛለን፡፡ አምባሳደር ሉካስ ዶሚንጎ በአፍሪካ ህብረት የኩባ አምባሳደር፣ የኮሎምቢያው አምባሳደር የይሶን አርካዲዮ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ እና የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ደንዚል ዳግላስ ጋር — ስለ ቅኝ ግዛት ካሳ፣ በአፍሪካ እና በካሪቢያን ሀገራት መካከል መፈጠር ስላለበት ትብብር እና አንድነት ውይይት አድርገናል፡፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0