ቦትሶዋና ሉዓላዊ የሀብት ፈንድ አቋቋመች
18:43 10.09.2025 (የተሻሻለ: 18:44 10.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቦትሶዋና ሉዓላዊ የሀብት ፈንድ አቋቋመች
ተነሳሽነቱን ይፋ ያደረጉት ፕሬዝደንት ዱማ ቦኮ፤ ፈንዱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የአልማዝ ሀብት ጥገኝነት ለመቀነስና የረዥም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
ቦኮ አክለውም ትልቅ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት፤ ፈንዱ "ጠንካራ እና ራዕይ ያለው" እርምጃ ነው ብለዋል፡፡
አልማዝ በቦትስዋና የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ያወሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢንዱስትሪው ተለዋዋጭነት ፈጣን ለውጥ እንደሚያስፈልግ ማሳያ ነው ብለዋል።
ብሔራዊ ተቋሙ በቦትስዋና ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስልታዊ የረጅም ጊዜ ቁጠባ እና ኢንቨስትመንቶች እንደሚውል ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X