የሩሲያ ጦር የዩክሬን ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማትን እንጂ በፖላንድ ዒላማዎችን አልመታም - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ጦር የዩክሬን ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማትን እንጂ በፖላንድ ዒላማዎችን አልመታም - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
የሩሲያ ጦር የዩክሬን ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማትን እንጂ በፖላንድ ዒላማዎችን አልመታም - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.09.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ጦር የዩክሬን ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማትን እንጂ በፖላንድ ዒላማዎችን አልመታም - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

"በጥቃቱ ጥቅም ላይ የዋሉት እና ወደ ፖላንድ ገብተዋል በሚል ክስ የቀረበባችው የሩሲያ ድሮኖች ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ መብረር አይችሉም፡፡"

ℹ የሩሲያ ጦር ትናንት ማምሻውን በዩክሬን ኢቫኖ ፍራንኮቭስክ፣ ክሜልኒትስኪ እና ዛሂቶሚር ክልሎች እንዲሁም በቪኒትሲያ እና ልቮቭ ከተሞች ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረሱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እነዚህ ወታደራዊ መሠረት ልማቶች ለዩክሬን ጦር ኃይሎች የውጊያ ተሽከርካሪዎችን እና የአቪዬሽን መሳሪያዎችን በማምረት እና በመጠገን እንዲሁም ሞተሮችን እና ድሮኖችን በማምረት ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

ጥቃቱ የረዥም ርቀት ድሮኖችን በሚያመርቱት ልቮቭ የጦር መሳሪያ እና ልቮቭ አውሮፕላን ፋብሪካ ላይም መፈፀሙ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ሁሉም የጥቃቱ ኢላማዎች መመታታቸውን ጠቁሟል። ወታደራዊ ክፍሉ አክሎም በቀረበው ክስ ዙሪያ ከፖላንድ የመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ምክክር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0