ስፑትኒክ ቤጂንግ ውስጥ 25ኛውን ዓለም አቀፍ ቢሮ ከፈተ

ሰብስክራይብ

ስፑትኒክ ቤጂንግ ውስጥ 25ኛውን ዓለም አቀፍ ቢሮ ከፈተ

ከሁሉም የምዕራባውያን ሚዲያዎች የበለጠ ሰፊ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሉት ስፑትኒክ ቻይና፤ በአዲሱ የቤጂንግ ቢሮ ለአስር ዓመታት የቆየውን ቆይታ ያጠናክራል እንዲሁም የሩሲያ-ቻይና ሚዲያ ትብብርን ስልታዊ በሆነ መንገድ ያሳድጋል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች፡-

ዲሚትሪ ኪሴሌቭ፤ የስፑትኒክ እናት ሚዲያ ቡድን ሮሲያ ሴጎድናያ ዋና ዳይሬክተር፣

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፣

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣

ታዋቂ የቻይና ሚዲያ አዘጋጆች እና ጦማሪዎች፡፡

ዲሚትሪ ኪሴሌቭ "ለበለጠ ንቁ ትብብር ዝግጁ ነን። እንደ ሁለት ታላላቅ ኃይሎች የዓለም የጋዜጠኝነት አዝማሚያዎችን መቅረጽ ያለብን እኛ ነን ብዬ አምናለሁ" ሲሉ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ በ10 ዓመታት ውስጥ በቻይና በጣም ውጤታማው የውጪ ሚዲያ መሆን ችሏል።

ማሪያ ዛካሮቫ ዝግጅቱ የቻይና ታዳሚዎችን ከፍ ያለ እምነት እና ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የከፍተኛ ደረጃ ትብብርን ያሳያል ብለዋል።

"ምዕራባውያን ዓለም አቀፉን የሚዲያ ምህዳር ለመቆጣጠር እና ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለመሸጥ ጥረት እያደርጉ ባለበት ወቅት፤ የመናገር ነጻነትን በፅናት መከላከላችን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን በጋራ መመከታችን አስፈላጊ ነው" ሲሉ አስረግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0