ደቡብ አፍሪካ እስራኤል ኳታር ላይ የፈፀመቸውን ጥሰት አወገዘች
13:32 10.09.2025 (የተሻሻለ: 13:34 10.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ እስራኤል ኳታር ላይ የፈፀመቸውን ጥሰት አወገዘች
በኳታር ዶሃ በንፁሃን ዜጎች ህንፃ ላይ በእስራኤል የተፈፀመው ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው ሲል የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ጥቃቱ የሃማስ ፖለቲካ ቢሮ ልዑኮችን ዒላማ አድርጓል ቢባልም የንፁሃንን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ ነው ሲልም አክሏል፡፡
"ይህ የኳታርን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት በግልፅ የጣሰው ጥቃት፤ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ወሳኝ የማመቻቸት ሚናን እየተጫወተ ከሚገኘው የኳታር መንግሥት ጥረት ተቃራኒ ነው" ሲል ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
ለኳታር ድጋፏን የገለፀችው ደቡብ አፍሪካ፤ ለሰላማዊ ንግግሮች የእስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲቆም በማሳሰብ፤ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች፡፡
የደቡብ አፍሪካ መግለጫ የአረብና የእስያ ሀገራትን ጨምሮ እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የባህረ ሰላጤ ትብብር ም/ቤት ያሉ በርካታ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ተቃውሞ ያስተጋባ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X