"ማንም አገር እንደተገለለ አይሰማውም፤ ጫናውን ብቻውን የሚሸከም አገርም የለም" የሶማሊያ ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ማንም አገር እንደተገለለ አይሰማውም፤ ጫናውን ብቻውን የሚሸከም አገርም የለም" የሶማሊያ ፕሬዝዳንት
ማንም አገር እንደተገለለ አይሰማውም፤ ጫናውን ብቻውን የሚሸከም አገርም የለም የሶማሊያ ፕሬዝዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.09.2025
ሰብስክራይብ

"ማንም አገር እንደተገለለ አይሰማውም፤ ጫናውን ብቻውን የሚሸከም አገርም የለም" የሶማሊያ ፕሬዝዳንት

በሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ሀሰን ሼክ መሃመድ ሕዳሴ ግድብ የጋራ ሀብት፣ የጋራ ወንድማማችነት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

"በዚህ ቀጣና ውስጥ ስለ ልማት ስንናገር፣ ስለፉክክር ሳይሆን ስለትብብር መነጋገር አለብን። ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳመለከቱት እና ቃል በገቡት መሠረት፤ ሁላችንም በሰላም አብሮ መኖር እና ብልጽግናን የማየት እጣ ፈንታ አለን" ሲሉ ግድቡ የሚያመጣውን ትብብር ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንቱ የአካባቢው ሀገራት ያለፈውን አስተሳሰብ በመተው ወደፊት የሚያራምዱ ትብብሮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

"የታችኛው እና የላይኛው ተፋሰስ አገሮች እንደ ማኅበረሰብ ስንሠራ ብቻ ነው መበልጸግ የምንችለው። " ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0