የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዓለምን በሙሉ ያስደነቀ ፕሮጀክት ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝደንት አወደሱ
20:38 09.09.2025 (የተሻሻለ: 21:04 09.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዓለምን በሙሉ ያስደነቀ ፕሮጀክት ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝደንት አወደሱ
በግድቡ ምርቃት ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ:
"ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው፡፡ ዓለምን በሙሉ ያስደነቀ ፕሮጀክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወዳጆችን በሙሉ ያስደሰተና ሀገር በድል ማጠናቀቋን ያበሰረ ነው" ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ታላቁ ግድቡን በመገንባት ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሳተፋቸው አስገራሚ ያሉት ፕሬዝደንቱ፣ ለምርቃት በመብቃቱም ደስ ብሎናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሁላችንም ደስ ብሎናል፡፡ ኢንጂነሩ ኢትዮጵያዊ፣ ቴክኒሺያኑ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የሚያስገረምና (ከዚህ ቀደም) ያልታየ ነው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በ2003 ዓ.ም ተጀምሮ በኢትዮጵያ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የፋይናንስ ምንጭነት ከ14 ዓመት በኋላ የተጠናቀቀ ፕሮጀክት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X