አብዛኛው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የናዚ አስተሳሰብን ለመዋጋት ከሩሲያ ጎን ይቆማል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
20:22 09.09.2025 (የተሻሻለ: 20:24 09.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አብዛኛው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የናዚ አስተሳሰብን ለመዋጋት ከሩሲያ ጎን ይቆማል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳሉት፤ ሩሲያ ባዘጋጀችው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ በናዚነት እና በናዚ አዲስ አስተሳሰብ (ኒዮ-ናዚዝም) ላይ የቀረበው ዓመታዊ የውሳኔ ሐሳብ ድምጽ ውጤት የዚህ ግልጽ ማስረጃ ነው።
በተመሳሳይ ጊዜ በአንዳንድ የምዕራባውያን አገሮች “የናዚን ቫይረስ የመከላከል አቅም ተዳክሟል”፡፡ በዚህም ምክንያት “የራሳቸውን ልዩነት፣ የብሔርተኝነት የበላይነት፣ የሩሲያ ጥላቻ እና የሴማዊያን ጥላቻ” ወደ ምን ሊመራ እንደሚችል ረስተዋል ሲሉ ላቭሮቭ በዓለም አቀፍ የፀረ-ፋሺስት መድረክ ላይ ተናግረዋል።
ላቭሮቭ የታሪክን እውነት መጠበቅ እና የናዚን ዝንባሌዎች ለማዳፈን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ መቀጠል የተቀደሰ ተግባር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X