ሕዳሴ ግድብ በራስ አቅም ከኢኮኖሚ ባርነት ነፃ መውጣት የመቻል ትዕምርት ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ሕዳሴ ግድብ በራስ አቅም ከኢኮኖሚ ባርነት ነፃ መውጣት የመቻል ትዕምርት ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የሕዳሴ ግድብ የውስጥ አቅምን በማስተባበር ግዙፍ የልማት ሥራዎችን እውን ማድረግ እንደሚቻል ለአፍሪካ አብነት መሆኑን መላኩ አለበል ገልፀዋል።

"ግድቡ እንደ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያካፈለ በመሆኑ የእኛ ብቻ ሳይሆን የቀጣናውም ጭምር ማለት እንችላለን። ይህም ኢትዮጵያን በቀጣናው ያላትን የኢኮኖሚ አስተዋጽኦ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል" ሲሉም ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ግድቡ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በአሕጉሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖሊሲ ነፃነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ፕሮጀክቶች በስፋት ሊተገበሩ እንደሚገባም አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0