"ይህ የምህንድስና አድዋ ነው" - የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ይህ የምህንድስና አድዋ ነው" - የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር
ይህ የምህንድስና አድዋ ነው - የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.09.2025
ሰብስክራይብ

"ይህ የምህንድስና አድዋ ነው" - የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር

በኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የተገኙት ሚያ አሞር፣ የኢትዮጵ ሕዝብ እና መንግሥት በግንባታው ሂደት ውስጥ ተቋቁመው ያለፉትን የፋይናንስ እና የዲፕሎማሲ ተግዳሮቶች አፅንኦት ሰጥተውበታል።

" ... ግድቡን ስንጎበኝ ወደ ወንድሜ ዞር ብዬ ይሄ የአድዋ የምህንድስና ሥራ ነው አልኩት" ሲሉ በግድቡ ግንባታ የተሰማቸውን ኩራት ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ የግድቡ ግንባታ ካረቢያንን ጨምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ዐይን ከፋች መሆኑን አስረድተዋል።

"የአድዋ ድል እነዚህ ነገሮች እንደሚቻሉ አስተማረን ... ዛሬ ከዚህ ስንወጣ የአፍሪካ መነቃቃትን በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል ብቻ ሳይሆን መላውን አኅጉር እና ዳያስፖራውንም እንድናይ እፀልያለሁ፤ ምክንያቱም ይህ ግድብ ማንኛውንም ሥራ መሥራት እንደምንችል አሳይቶናል።" ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0