ኢትዮጵያውያን የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ ደስታቸውን ሲገልፁ ውለዋል
18:47 09.09.2025 (የተሻሻለ: 18:54 09.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ ደስታቸውን ሲገልፁ ውለዋል
ግድቡ ቀደምት አባቶች በቁጭት ያዜሙለት፣ ሕጻናት ልጅ ሆነው ያለሙት፣ አዛዉንቶች ለልጆቻቸው ሊያወርሱት የጓጉለት እና በትብብር ሕያው የሆነ ብሔራዊ አርማ ተደርጎ ይታሰባል፡፡
በጉባ በነበረው የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በጥቁር ሕዝብ ታሪክ ታላቅ ሥራ ነው” ያሉትን ግድብ “ባለቤቶች የሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና አፍሪካውያን” እንዲጎበኙት ጥሪ አቀርበዋል።
ለግድቡ ግንባታ ከወጣው 233 ቢልዮን ብር አጠቃላይ ወጪ ኢትዮጵያዊያን፣ በቦንድ ግዢ 18.9 ቢልዮን ብር፣ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን 1.6 ቢልዮን ብር፣ በስጦታ 3.2 ቢልዮን ብር አበርክተዋል፡፡
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X





