የኔፓል የፖለቲካ ቀውስ፡ እስካሁን የምናውቀው ነገር
የኔፓል የፖለቲካ ቀውስ፡ እስካሁን የምናውቀው ነገር
⭕ መንግሥት በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ መደረኮች ላይ እገዳ ከጣለ በኋላ ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።
⭕ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻርማ ኦሊ የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ቢጠሩም ሕዝባዊ አመፁ እየተባባሰ ቀጥሏል፡፡
⭕ ተቃዋሚዎቹ ሲቃረቡ ሰራዊቱ ሚኒስትሮችን በሄሊኮፕተር አሽሽቷል።
⭕ የጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የፕሬዝዳንቱን መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም የገዢው ኔፓል ኮንግረስ ዋና መሥሪያ ቤትን አቃጥለዋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
⭕ ካታማንዱ ትሪቡቫን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተዘጋ ሲሆን ሁሉም በረራዎች ተሰርዘዋል።
⭕ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሊን ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል እርሳቸውም ተስማምተው ለቀዋል።
⭕ ነጠኞቹ ፓርላማውን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን፣ የፕሬዝዳንቱን ጽሕፈት ቤት፣ የገዢው ፓርቲ ዋና መሥሪያ ቤት እና የመንግሥት ግቢን አቃጥለዋል።
⭕ በግርግሩ 22 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል ሲል ኢንዲያ ቱዴ ዘግቧል።
⭕ ተቃዋሚዎች በእስር ላይ የነበሩትን የተቃዋሚ መሪ ራቢ ላሚቻኔን ሲያስፈቱ 1 ሺህ 500 እስረኞችም ከናኩ እስር ቤት አምልጠዋል።
⭕ ታሪካዊው የመንግስት መኖሪያ ቤት ሲንጋ ዱርባር ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጉዳት እንደደረሰበት ተዘግቧል።
⭕ ከኔፓል ግዙፍ መገናኛ ብዙሃን አንዱ የሆነው ካንቲፑር ሚዲያ ግሩፕ በእሳት ተቃጥሏል።
⭕ የኔፓል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼር ባሃዱር ዴውባ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አርዝ ራና ዴውባ በተቃዋሚዎች ከፍተኛ ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ከላይ የተያያዘዉ ቪዲዮው፤ በካታማንዱ የሚገኘው የቢሬንድራ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል እየተቃጠለ ባለበት ሁኔታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በውጭ ሲሰባሰቡ ይታያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X