የብሪክስ መሪዎች ዛሬው ባካሄዱት ልዩ ስብሰባ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ንግግር አድርገዋል

የብሪክስ መሪዎች ዛሬው ባካሄዱት ልዩ ስብሰባ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ንግግር አድርገዋል
መሪዎቹ ያነሷቸውን ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦች ይመልከቱ
የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ ፦
ለዩክሬን ግጭት ዕልባት ሁሉንም ወገኖች የደህንነት ስጋቶች ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአላስካው ስብሰባ ወደ ሰላም የተደረገ እርምጃ ነበር ብለዋል፡፡
ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀቦች በሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን የማሳደግ ዕድሎችን እያቀቡ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፦
ብሪክስ ለዓለም አቀፍ ፍትሕ መቆም እንዳለበት ሺ ጂንፒንግ ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ዓለም አቀፍ ሁከትን ተቋቁሞ በዘላቂ እና የረዥም ጊዜ እድገት መንገድ ላይ እንደሚፀና ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ሺ የዩክሬን ቀውስን በተመለከተ ለብራዚል አቋም ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብልደል ፈታህ ኤል-ሲሲ፦
የግብጹ ፕሬዝዳንት በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ያለው እምነት እየተሸረሸረ ነው ብለዋል፡፡
ምክንያቱ፡ ግጭቶችን ዕልባት ለመስጠት ያለው ሚና መወጣት አለመቻሉ ነው፡፡
በአንጻሩ ብሪክስ በጋራ መከባበር ላይ የተመሠረተ ገንቢ ትብብርን ያለማቋረጥ ያበረታታል ብለዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፦
በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ሥር ነቀል ለውጦች እየተካሄዱ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
ለውጦቹ የዓለምን ኢኮኖሚ እንደገና ለማደራጀት ሁለቱንም ማለትም ተግዳሮቶች እና እድሎችን ያመጣሉ፡፡
ዓለም ከነጠላ ወደ ብዝኃ ዋልታ ሥርዓት እየተሸጋገረች ነው፤ በዚህ ሽግግር ብሪክስ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ አክለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X