በኬንያ ሳምቡሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የከዋክብት የቱሪዝም እንቅስቃሴ ተጀመረ
20:25 08.09.2025 (የተሻሻለ: 20:34 08.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኬንያ ሳምቡሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የከዋክብት የቱሪዝም እንቅስቃሴ ተጀመረ
ሀገሪቱ በትናንትናው ዕለት በሳምቡሩ ካውንቲ የከዋክብት የቱሪዝም እንቅስቃሴን ከሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ጋር በተጣጣመ መልኩ ይፋ አድርጋለች።
ጎብኝዎች ሚልኪ ዌይን እየተመለከቱ ኮከብ ማየት፣ የጥንት የሳምቡሩ የኮከብ ታሪኮችን መስማት እንዲሁም የሰሜናዊውንና የደቡባዊውን የምድር ክፍል ሰማይን መመልከት ይችላሉ፡፡
የቱሪዝም እና የዱር አራዊት ካቢኔ ፀሐፊ ርብቃ ሚያኖ ተነሳሽነቱን አድንቀዋል።
“የከዋክብት ቱሪዝም አዲስ ምርት ብቻ ሳይሆን ለውጥ የሚያመጣ እድል ነው። እንደ ሳምቡሩ ያሉ ድብቅ ቦታዎችን በማስተዋወቅ የሥራ ዕድል እንፈጥራለን፤ የአካባቢን ኩራት እናጎላለን፤ እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ የሰማያት ጠባቂዎች እንዲሆኑ እናግዛለን” ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።
የፕሬዝዳንት ሩቶ ‘የታችኛው ኢኮኖሚ ለውጥ አጀንዳ’ አካል የሆነው ይህ ፕሮጀክት፣ ኬንያ እስከ 2027 ድረስ 5 ሚሊዮን ጎብኝዎችን ለመሳብ ያላትን ዓላማ ይደግፋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia