ሩሲያ በቀል አትፈልግም፤ ነገር ግን ምዕራባውያንን የፈፀሟቸውን ድርጊቶች ከግምት ውስጥ ታስገባለች ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በቀል አትፈልግም፤ ነገር ግን ምዕራባውያንን የፈፀሟቸውን ድርጊቶች ከግምት ውስጥ ታስገባለች ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
ሩሲያ በቀል አትፈልግም፤ ነገር ግን ምዕራባውያንን የፈፀሟቸውን ድርጊቶች ከግምት ውስጥ ታስገባለች ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.09.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በቀል አትፈልግም፤ ነገር ግን ምዕራባውያንን የፈፀሟቸውን ድርጊቶች ከግምት ውስጥ ታስገባለች ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

“የቀድሞ የምዕራባውያን አጋሮቻችን የአሁን ጎረቤቶቻችን ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ወደ ሩሲያ መጥተው እንደገና መሥራት ሲፈልጉ አንገፋቸውም” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሞስኮ ስቴት ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲትዩት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል።

የላቭሮቭ ዋና ዋና ግግሮች፦

ምዕራባውያን የሩሲያን የኃይል ሃብቶች እንድትተው የሚያቀርቡት ጥያቄ የሞስኮን አጋሮች ኢኮኖሚ እየጎዳ ነው።

ምዕራባውያን ለዘመናት ከኖረ ታሪክ በመነሳት ሩሲያን መግዛት እንደማይቻል መደምደሚያ ላይ አለመድረሳቸው አስደናቂ ነው።

ሩሲያ እና አሜሪካ የጋራ የኢኮኖሚ ጥቅሞች ሊኖራቸው ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት፣ በአርክቲክ እና በሕዋ ዘርፎች ላይ መሥራት ይገኙበታል።

ሞስኮ ከአሜሪካ ጋር እኩል አጋርነት ለመፍጠር ፍላጎት ያላት ሲሆን አሜሪካም በበኩሏ ተመሳሳይ ፍላጎት እያሳየች ነው።

ትራምፕ የዩክሬን ቀውስ በተሳታፊዎቹ ብሔራዊ ህጋዊ ጥቅሞች ላይ ተመስርቶ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት የሚገልጽ ግንዛቤ እያሳዩ ነው።

ዋሽንግተን የዩክሬን ግጭት ዋነኛ መንስኤዎችን በተመለከተ የሩሲያን አቋም ማድመጥ ጀምራለች።

የብሪክስን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገለልተኛ የክፍያ ሥርዓቶችን የማልማት ሥራ ቀጥሏል።

ሩሲያ ላለመነጋገር አጥር እየገነባች አይደለም ፤ ከሁሉም ጋር እኩል በሆነ ደረጃ ለውይይት ዝግጁ ናት።

ከዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ጅማሮ አንስቶ ሩሲያ “ኢኮኖሚያዊ ውድቀት” ይገጥማታል ተብሎ ቢተነብይም ቁጥራዊ መረጃዎች ግን ተቃራኒውን አሳይቷል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0