ዓለም ከነጠላ ወደ ብዝኃ ዋልታነት ሥርዓት እየተሸጋገረች ነው ሲሉ ራማፎሳ ተናገሩ
17:41 08.09.2025 (የተሻሻለ: 17:44 08.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዓለም ከነጠላ ወደ ብዝኃ ዋልታነት ሥርዓት እየተሸጋገረች ነው ሲሉ ራማፎሳ ተናገሩ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ እየታዩ ያሉ ትልልቅ ለውጦች የዓለምን ኢኮኖሚ እንደገና ለመቅረፅ የሚያስችሉ ተግዳሮቶችን እና እድሎችን እየፈጠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የራማፎሳ ዋና ዋና ግግሮች ፦
🟠 ደቡብ አፍሪካ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች፤ የብሪክስ አገሮችም በድርጅት ደረጃ ለሚደረገው ለውጥ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
🟠 የብሪክስ አገሮች ባለብዙ ወገን ተቋማትን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት "ግንባር ቀደም" ናቸው።
🟠 ብሪክስ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን በመቅረፅ፣ ድህነትን በመዋጋት እና ብዝኃ ወገንነተን በማስጠበቅ ረገድ ያለውን ሚና ማሰብ አለበት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X