አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ የ160 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ክፍተት ብቻዋን መሸከም አትችልም - የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ የ160 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ክፍተት ብቻዋን መሸከም አትችልም - የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን
አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ የ160 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ክፍተት ብቻዋን መሸከም አትችልም - የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.09.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ የ160 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ክፍተት ብቻዋን መሸከም አትችልም - የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን

በ13ኛው የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚስኑ ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ አስቸኳይ፣ ሊተነበይ የሚችል እና መጠነ ሰፊ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።

"እኛ የተሰባሰብነው ለሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ (ACS2) እና ለመንግስታቱ ድርጅት የአየር ለውጥ ጉባኤ (COP30) የአፍሪካ የጋራ ድምፅ መሠረት ለመጣል ነው። እና ዛሬ የምንዘጋው ወጥ የሆነና ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የሆነ የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ ይዘን ነው" ሲሉ አክለዋል።

የአፍሪካን አግባብ ያልሆነ የብድር ወጪን ለመቀነስ፣ ዕዳን ለመሰረዝ ወይም የክፍያ ጊዜውን ለማስተካከል እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ የአኅጉሪቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች የመዋቅር ለውጥ እንዲፈጠር በጉባኤው ጥሪ ቀርቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0