የአዘርባጃን የቀድሞ ወታደር በሩሲያ ከዩክሬን ጋር በተገናኙ የሽብር ጥቃቶች ተጠርጥሮ መያዙን የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አስታወቀ

ሰብስክራይብ

የአዘርባጃን የቀድሞ ወታደር በሩሲያ ከዩክሬን ጋር በተገናኙ የሽብር ጥቃቶች ተጠርጥሮ መያዙን የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አስታወቀ

አገልግሎቱ (ኤፍኤሲቢ) እንደገለጸው፣ ከዩክሬን ባልደረቦች መመሪያ በመቀበል ሲሠራ የነበረው የአዘርባጃን ዜጋ በደቡባዊ የሩሲያ ከተማ በስታቭሮፖል ተይዟል።

ከዚህ ቀደም በአዘርባጃን የጦር ኃይሎች ልዩ ክፍል ውስጥ ያገለገለው ግለሰቡ፣ የደህንነት ኤጀንሲዎችን ሕንጻዎች ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ለማካሄድ በርካታ ፈንጂዎችን ለመሥራት አስቦ እንደነበር ኤፍኤስቢ ገልጿል።

በተጠርጣሪው ላይ ሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት የማድረግ የወንጀል ክስ ተከፍቷል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0