ለጤናማ እና ዘላቂነት የምግብ አቅርቦት የአግሪኮሎጂ ፈጠራ አስፈላጊ ነው - የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት አስተባባሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለጤናማ እና ዘላቂነት የምግብ አቅርቦት የአግሪኮሎጂ ፈጠራ አስፈላጊ ነው - የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት አስተባባሪ
ለጤናማ እና ዘላቂነት የምግብ አቅርቦት የአግሪኮሎጂ ፈጠራ አስፈላጊ ነው - የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት አስተባባሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.09.2025
ሰብስክራይብ

ለጤናማ እና ዘላቂነት የምግብ አቅርቦት የአግሪኮሎጂ ፈጠራ አስፈላጊ ነው - የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት አስተባባሪ

አስተባባሪው ሚሊዮን በላይ(ዶ/ር) አኅጉሪቱ ወደ ጤናማ እና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ለመሸጋገር፣ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ጤናማ፣ ገንቢ፣ ዘላቂ በሆነ መንገድ የተመረተ እና ተስማሚ የሆነ ምግብ ለማምረት የሚያስችሉ መንገዶት ላይ ትኩረት መስጠት አለባቸው ብለዋል።

አስተባባሪው በአግሪኮሎጂ የሥራ ፈጠራ ውድድር ወቅት ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቆይታ የምግብ ሥርዓት ላይ ተግባራዊ የሚሆን ቴክኖሎጂ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

"አርሶ አደሮቻችን በተቻለ መጠን ብዛት ያላው ጤናማ ምግብ እንዲያመርቱ የሚረዳ ቴክኖሎጂ ማምረት አለብን። በተጨማሪም፣ የሚፈጀው የጉልበት መጠን በተቻለ መጠን እንዲቀንስ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

የጥምረቱ አስተባባሪ የአፍሪካ ሀገር በቀል ምግቦች አስፈላጊነት  ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።

"በጣም ጤናማ እንዲሁም ከባሕል አንፃር ተስማሚ ናቸው። ለሕዝቦች ማንነትም በጣም አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ ገልፀዋቸዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0