የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶ አደሮች 5.6 ቢሊዮን ብር ብድር እና 6.8 ቢሊዮን ብር የእርሻ መሣሪያዎችን አስገኝቷል - ግብርና ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶ አደሮች 5
የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶ አደሮች 5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.09.2025
ሰብስክራይብ

የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶ አደሮች 5.6 ቢሊዮን ብር ብድር እና 6.8 ቢሊዮን ብር የእርሻ መሣሪያዎችን አስገኝቷል - ግብርና ሚኒስቴር

በግብርና ሚኒስቴር በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም በለማው የዲጅታል ሥርዓት 30 ሚሊዮን ማሳዎች እና 9 ሚሊዮን ባለይዞታዎች በዲጂታል ሥርዓት የተመዘገበ የመሬት አጠቃቀም መብት እንዲኖራቸው አስችሏል ተብሏል።

ለሰባት ዓመታት በተተገበረው የብሔራዊ ገጠር መሬት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ተጨማሪ ስኬቶችም ተጠቅሰዋል፦

ወደ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ የመሬት ግብይት መብት አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

ከ20 በላይ አበዳሪ የፋይንስ ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትን እንደ ብድር ዋስትና እንዲቀበሉ አስችሏል፡፡

አርሶ አደሮች 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር አግኝተዋል፡፡

6.8 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የእርሻ መሣሪያዎችን አግኝተው መጠቀም ችለዋል፡፡

የቡና ኤክስፖርት ላይ የተቀመጠውን አስገዳጅ ሁኔታዎች ለማሟላት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

የመረጃ ሥርዓቱ በ10 ክልሎች፣ በ70 ዞኖች፣ በ516 ወረዳዎች እና በ13 ሺህ በላይ ቀበሌዎች ተደራሽ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0