ብሪክስ የዓለም አቀፍ አስተዳደርን እንደገና ለመገንባት አልሟል ሲሉ ኢኳዶራዊው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ገለፁ
12:28 08.09.2025 (የተሻሻለ: 12:34 08.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሪክስ የዓለም አቀፍ አስተዳደርን እንደገና ለመገንባት አልሟል ሲሉ ኢኳዶራዊው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሪክስ የዓለም አቀፍ አስተዳደርን እንደገና ለመገንባት አልሟል ሲሉ ኢኳዶራዊው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ገለፁ
የብሪክስ አባል ሀገራት ስምምነቶቻቸውን በተለይም በንግድ እና በደህንነት ዘርፍ ዘመናዊ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ሉዊስ ማርቻን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ሰፊውን የብሪክስ ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የተለየ የንግድ መንገድ ያስፈልገናል። ይህ የሚሆነው እውነተኛ የመገበያያ ገንዘብ በመጠቀም እና የዶላር የበላይነት መቀልበሻ ስንፈጥር ነው፡፡ ” ብለዋል።
እንደ ባለሙያው፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ብዝኃ ዓለምን መቀበል አለባቸው፡፡ በተለይም፦
🟠 የተባበሩት መንግሥታት፣
🟠 የአሜሪካ መንግሥታት ድርጅት እና
🟠 የኢንተር-አሜሪካ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሻንጋይ ትብብር ድርጅት+ ጉባኤ ወቅት ለአዲስ ዓለም አቀፍ አስተዳደር አምስት ነጥብ ያለው እቅድ አቅርበዋል።
ብራዚል በዛሬው ዕለት የአሜሪካን የንግድ ፖሊሲ በተመለከተ ለመወያየት ልዩ የብሪክስ የበይነመረብ ጉባኤን ታስተናግዳለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X