ኢትዮጵያ እና ባሃማስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመሥረት ተስማሙ
11:50 08.09.2025 (የተሻሻለ: 11:54 08.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ባሃማስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመሥረት ተስማሙ
እየተካሄደ ካለው ሁለተኛው የአፍሪካ እና ካሪቢያን ማኀበረሰብ አገራት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ እና የባሃማስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬድሪክ ኦድሊ ሚቼል ጋር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ከውይይቱ በኋላ ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ እና ባሃማስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመሥረት የሚያስችላቸውን ሥምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ እና ባርባዶስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመሥረት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X