በካሪቢያን ቀጣና “የካሳ ፍትሕ አስፈላጊነት እጅግ በጣም ግልጽ ነው” - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
19:51 07.09.2025 (የተሻሻለ: 19:54 07.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በካሪቢያን ቀጣና “የካሳ ፍትሕ አስፈላጊነት እጅግ በጣም ግልጽ ነው” - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በሁለተኛው የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት፣ የሴንት ኪትስና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ እና የኢኮኖሚ ልማትና ንግድ ሚኒስትር ዴንዝል ዳግላስ ካሪቢያውያን ገና በልጅነታቸው ጅምሮ ስለ ባርነት ጭካኔዎች እንደሚማሩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
የሴንት ኪትስና ኔቪስ በጎርጎሮሳውያኑ 1983 ከታላቋ ብሪታንያ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ተራማጅ ሆናለች፤ በባርነት ምክንያት የሆኑ የሰው ልማት መዘግየቶች ለመቅረፍ የሚያስፈልገውን ፍትሕ ለማስፈን ፍላጎት እንዳላትም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
ዳግላስ “በአፍሪካ ሕብረት እና በሕብረቱ ኮሚሽን፣ በራሳችን ድርጅት፣ በካሪቢያን ማኅበረሰብ በኩል ከአፍሪካ ጋር በቅርበት በመተሳሰር ከተፈፀሙብን ታሪካዊ ግፎች ተሻግረን ወደ ታሪካዊ ልማት የምንጓዝበት ጊዜ እንደሆነ እናምናለን፡፡” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ፣ እውነተኛ ካሳ ማለት ነጻነትን ማጠናከር እና በጋራ ወደፊት መጓዝ፣ የኢኮኖሚ ልማት ሐሳቦችን መለዋወጥ እና የትራንስፖርት ትስስሮችን ማሻሻል መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X