ለኢትዮጵያ ፋሽን ዓለም አቀፍ ዕድል የከፈተው የሞስኮ ብሪክስ ፕላስ የፋሽን ጉባኤ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለኢትዮጵያ ፋሽን ዓለም አቀፍ ዕድል የከፈተው የሞስኮ ብሪክስ ፕላስ የፋሽን ጉባኤ
ለኢትዮጵያ ፋሽን ዓለም አቀፍ ዕድል የከፈተው የሞስኮ ብሪክስ ፕላስ የፋሽን ጉባኤ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.09.2025
ሰብስክራይብ

ለኢትዮጵያ ፋሽን ዓለም አቀፍ ዕድል የከፈተው የሞስኮ ብሪክስ ፕላስ የፋሽን ጉባኤ

የፋሽን ጉባኤው ለአፍሪካን የፋሽን ዕድገት፣ ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ አጉልቶ ያሳየ መሆኑን የኢትዮጵያ ልዑካን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

በጉባኤው ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው የ“ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ሳምንት” መሥራች ማሕሌት ተክለማርያም “በብሪክስ ፕላስ ፋሽን ጉባኤ ላይ የተፈጠሩት ግንኙነቶች ትብብርን ለማሳደግ እና የኢንዱስትሪዎቻችንን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው” ብላለች፡፡

ማሕሌት፣ ጉባኤው ለእውቀት ሽግግር፣ ቁልፍ ጥምረቶችን ለመፍጠር እንዲሁም የአፍሪካን ፋሽን ዓለም አቀፍ ቁመናን ለማሳደግ ትብብሮችን ለመለየት እንደ ስትራቴጂያዊ መድረክ ማገልገሉንም ገልጻለች፡፡

የፋሽን ጉባኤው በነሐሴ ወር መጨረሻ በሞስኮ ሲካሄድ ከ60 በላይ ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ተሳታፊዎች ተሳትፍውበታል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0