በአንድ ወቅት ችላ ተብለው የነበሩ ድምፆች አሁን እንዲሰሙ እየጠየቁ ነው - ዐቢይ አሕመድ
14:28 07.09.2025 (የተሻሻለ: 14:34 07.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአንድ ወቅት ችላ ተብለው የነበሩ ድምፆች አሁን እንዲሰሙ እየጠየቁ ነው - ዐቢይ አሕመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው ሁለተኛው የአፍሪካ እና የካሪቢያን ማሕበረሰብ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠሙ ለሚገኙ ፈተናዎች የጋራ ድምጽ ማሰማት ይገባል ብለዋል፡፡
"ዓለም እየተለወጠች ነው፤ ቀደም ሲል ችላ ተብለው የነበሩ ድምፆች አሁን እንዲሰሙ እየጠየቁ ነው። በዚህ አዲስ ዘመን በተበታተነ መንገድ መናገር አንችልም፤ እንደ አንድ ሆነን መናገር አለብን" ሲሉ የትብብር አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተናጠል ሐሳብን ከመግለጽ ይልቅ አንድነት ኃይል መሆኑን በመገንዘብ በጋራ ድምጽ ማሰማት ይጠበቅብናል ብለዋል። የኢትዮጵያው መሪ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብየመተባበር ጥንካሬ ውጤት ማረጋገጫ አድርገው በአብነት ጠቅሰውታል፡፡
"በብዙ ሚሊዮን ልቦች ውስጥ የተወለደ፣ በራሳችን ሕዝብ የተደገፈ፣ በጉልበታቸውና በልዩ መስዋዕትነታቸው የተገነባ ነው። ለጋራ ራዕይ፣ ቁርጠኝነት እና የጋራ ጥረት ማሳያ እንዲሁም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካም ታሪካዊ ስኬት ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለአራት ቀናት የሚቆየው ጉባኤ የቅኝ ግዛት እና የባሪያ ንግድ የካሳ ፍትሕን እውን ከማድረግ ባሻገር፣ በአፍሪካ እና በካሪቢያን ሀገራት መካከል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም መስኮች አኅጉር ለአኅጉር ትበብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይመክራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X