ከቀውስ ወደ ተስፋ፤ የእናቶች ሞት ከመቶ ሺህ 871 ከነበረበት ወደ 195 ቀንሷል - አደም ፋራህ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከቀውስ ወደ ተስፋ፤ የእናቶች ሞት ከመቶ ሺህ 871 ከነበረበት ወደ 195 ቀንሷል - አደም ፋራህ
ከቀውስ ወደ ተስፋ፤ የእናቶች ሞት ከመቶ ሺህ 871 ከነበረበት ወደ 195 ቀንሷል - አደም ፋራህ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.09.2025
ሰብስክራይብ

ከቀውስ ወደ ተስፋ፤ የእናቶች ሞት ከመቶ ሺህ 871 ከነበረበት ወደ 195 ቀንሷል - አደም ፋራህ

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 2ኛው የአፍሪካ እና የካሪቢያን የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ መንግሥት በአንደኛ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ማድረጉን አስታውቀዋል።

“ባለፉት ዓመታት በሚወልዱ እናቶች፣ በአራስ ቤት ሕጻናት እና በሕጻናት ጤና ማሻሻል ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተናል፡፡ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ከ100 ሺህ እናቶች 871 ከነበረበት በጎርጎሮሳውያኑ 2000 ወደ 195 ቀንሷል፡፡” ብለዋል፡፡

አክለውም የአራስ ሕጻናት መጠነ ሞት እ.ኤ.አ. በ2000 በሕይወት ከሚወለዱ 1 ሺህ ጨቅላዎች 39 የነበረው ሞት፣ በ2022 ወደ 26 ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ ለውጥ እንዲመጣ ያስቻሉትን የጤና ኢንቨስትመንቶችንም ጠቅሰዋል

17 ሺህ የማኅበረሰብ ጤና ኬላዎች፣

ከ450 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና

4 ሺህ የጤና ማዕከላትን ተገንብተዋል።

እየተተገበረ ያለው የማኅበረሰብ የጤና መድኅን አገልግሎት 80 በመቶ ለሚሆነውን የሀገሪቱ ህዝብ ተደራሽ መሆኑን ተናግረዋል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0