የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የባህረኞች የስልጠና ማዕከል ተመረቀ
23:04 06.09.2025 (የተሻሻለ: 23:14 06.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የባህረኞች የስልጠና ማዕከል ተመረቀ
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባው ማዕከሉ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
ኢትዮጵያ የቀደመ የቀይ ባህር ስመ ገናናነቷን ለመመለስ የባህር በር ባለቤት ከመሆን ጀምሮ ዘረፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች እንደምትገኝ እና ማዕከሉ የዚህ ጥረት አንድ አካል መሆኑ በምረቃው ወቅት ተነግሯል።
በመርከብ ቅርፅ የተገነባው የስልጠና ማዕከል ግንባታ በሁለት አመት ተኩል መጠናቀቁ መከላከያ ሚኒስቴር ባሰራጫው ዘገባ አስታዉቋል።
ማዕከሉ የሰራዊት መኖሪያ ህንፃዎችን ፣መማሪያ ክፍሎችን ፣ በኤሌክትሮ መካኒክ የሚሰራ መመገቢያ አዳራሽ ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዬም እና ሌሎችንም ግንባታዎች አካቶ ይዟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X