ጊኒ በዳታ ማዕከል እና በብሔራዊ የመረጃ ቋት የዲጂታል ሉዓላዊነቷን አጠናከረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጊኒ በዳታ ማዕከል እና በብሔራዊ የመረጃ ቋት የዲጂታል ሉዓላዊነቷን አጠናከረች
ጊኒ በዳታ ማዕከል እና በብሔራዊ የመረጃ ቋት የዲጂታል ሉዓላዊነቷን አጠናከረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.09.2025
ሰብስክራይብ

ጊኒ በዳታ ማዕከል እና በብሔራዊ የመረጃ ቋት የዲጂታል ሉዓላዊነቷን አጠናከረች

የጊኒ የቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ከ600 ስኩዌር ሜትር በላይ ስፋት ያለው እና ጠንካራ የዲጂታል ደህንነት ሥርዓት የታጠቀው ብሔራዊ የዳታ(የመረጃ ክምችት) ማዕከል፤ ሀገሪቱ “ስትራቴጂያዊ ዲጂታል ዳታዋን እንድትጠብቅ፣ እንድትቆጣጠር እና እንድታስተዳድር” ያስችላታል።

ከዚህ ቀደም ይህ የመረጃ ክምችት በውጭ አገር  የሚተዳደር ስለነበር በየዓመቱ ወደ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ይደረግበት ነበር።

የ.ጂኤን (GN) ብሔራዊ የበይነመረብ ዶሜይን አሁን ለሁሉም ጊኒያውያን ክፍት ተደርጓል፡፡ ለዲጂታል ዳታ ቀለል ያለ እና አስተማማኝ መዳረሻን የሚሰጥ እንዲሁም የሀገሪቱን የዲጂታል ማንነት ከዓለምአቀፍ ሥነ-ምሕዳር ጋር ሙሉ በሙሉ የሚያዋህድ ነው።

መንግሥት በዚህ መሠረተ ልማት የመረጃ ሥርዓቶችን ደህንነት፣ አስተማማኝነት እና ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ የዲጂታል አብዮት መጀመሩን አረጋግጧል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0