ቻይና እና ሩሲያ የደቡባዊ ዓለም ትብብር መሪ ለመሆን ተዘጋጅተዋል - ባለሙያ
18:51 06.09.2025 (የተሻሻለ: 18:54 06.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻይና እና ሩሲያ የደቡባዊ ዓለም ትብብር መሪ ለመሆን ተዘጋጅተዋል - ባለሙያ
በቻይና እና ሩሲያ መካከል ያለው አጋርነት በተለይም በኢነርጂ ዘርፍ የጋራ መተጋገዝ ላይ የተመሠረተ መሆኑን የቻይና ሕዝቦች ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዤንግ ሺንዬ ከምስራቃዊ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ ተናገሩ።
ይህ ትብብር ለሁለቱ ሀገራት ብቻ ሳይሆን በአቅራቢዎች እና በተጠቃሚዎች ዘንድ ያለውን ያለመተማመን በመቀንስ በዓለም አቀፍ የኃይል ገበያ ላይ መረጋጋት የሚያመጣ ነው።
ቻይና እና ሩሲያ እነደ ዓለም ኃያላንነታቸው፣ ሰላምን በማስፋፋት እና የኃይል፣ የምግብ ዋስትና እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ ታዳጊ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥተዋል። ሁለቱም ሀገራት በእነዚህ ወሳኝ ዘርፎች እስያን፣ አፍሪካን እና ላቲን አሜሪካን የመደገፍ ዓላማ እንዳላቸው ባለሙያው ገልፀዋል።
እንደ ዤንግ ሺንዬ ገለጻ፣ በቻይና እና በሩሲያ መካከል የቀጠለው አጋርነት እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ባሉ የረቀቁ መስኮች ላይ የትብብር በር የሚከፍት ሲሆን ይህም በዚህ ወሳኝ ቴክኖሎጂ ውስጥ ያለውን ዓለም ክፍተት ለመሙላት ሊያግዝ ይችላል፡፡
“ቻይና እና ሩሲያ እንደ ዋና ዋና ኃያላን እና ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ሀገራት፣ ለዓለም ታላቅ ነገርን፣ መልካም ነገርን በማድረግ እና አዎንታዊ ለውጥ ለመፍጠር የሚችሉ ሥራዎችን የመሥራት አቅም አላቸው” ሲሉ ዤንግ ሺንዬ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X