ወጣቶችን ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት እንዲሠሩ ያነሳሳ የፈጠራ ውድድር
18:22 06.09.2025 (የተሻሻለ: 18:24 06.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ወጣቶችን ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት እንዲሠሩ ያነሳሳ የፈጠራ ውድድር
በፈጠራ መር የአግሮኢኮሎጂ ሥራ ፈጣሪዎች ላይ ያተኮረ እና “ምግቤ አፍሪካዊ ነው / ምግቤ ኢትዮጵያዊ ነው” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የግብርና ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ 72 አመልካቾች ከ11 ክፍለ ከተሞች የተሳተፉ ሲሆን 43 ለየት ያሉ ሐሳቦች ቀርበውበታል።
“ወደ አባቶቻችን የምግብ ሥርዓት እንመለሳለን” ሲል የውድድሩ አሸናፊ የአግሪኢኮሎጂ ባለሙያው ክሩቤል ኃይለሥላሴ ተናግሯል።
ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገቡት ሦስት የፈጠራ ሥራዎች የገንዘብ ሽልማት ያገኙ ሲሆን፣ ሁሉም ለቀጣይ ድጋፍ እና ለወደፊት ዕድሎች ግምት ውስጥ ይገባሉ።
በውድድሩ የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች ተግባር ላይ ከዋሉ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የግብርና ተግዳሮቶች ከ70 እስከ 86 በመቶ ሊፈቱ ይችላሉ ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X