የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች በሱዳን ኤል-ፋሸር በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል የተመድ ተልዕኮ አስታወቀ
15:25 06.09.2025 (የተሻሻለ: 15:34 06.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች በሱዳን ኤል-ፋሸር በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል የተመድ ተልዕኮ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች በሱዳን ኤል-ፋሸር በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል የተመድ ተልዕኮ አስታወቀ
እንደ የእውነታ አፈላላጊ ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ ቻንዴ ኦስማን፣ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ የፈጸማቸው ድርጊቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
የጅምላ ግድያ፣
ፆታዊ ጥቃት፣
ዘረፋ እና
ውድመት እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎች ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እና ጭፍጨፋን አስከትሏል።
የተፈፀመውን በደልን ለመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ቡድን ሪፖርቱን ከ200 በሚበልጡ ቃለመጠይቆች፣ የቪዲዮ ማስረጃዎች እና ከሲቪል ድርጅቶች በደረሰው መረጃ ላይ መሠረት አድርጓል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤል-ፋሸር፣ በሰሜን ዳርፉር የሱዳን ጦር የመጨረሻ ምሽግ እና አሁን ባለው ግጭት የፊት መስመር ላይ ከበባ ውስጥ ይገኛሉ።
“የጭካኔ ጦርነት” ተብሎ የተሰየመው ባለ 18 ገጽ ሪፖርት፣ ፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ እና አጋሮቹ አስፈላጊ የምግብ እና የሕክምና እርዳታን በመከልከል ርሃብን እንደ ጦር መሣሪያ እየተጠቀሙበት ነው ሲል ከሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X