በፌደራል ፖሊስ የተመደቡ ዘመናዊ የጥበቃ ጀልባዎች በንጋት ሐይቅ ላይ ቅኝት እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

በፌደራል ፖሊስ የተመደቡ ዘመናዊ የጥበቃ ጀልባዎች በንጋት ሐይቅ ላይ ቅኝት እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ

የመከላከያ ኢንጂኔሪንግ እንደገነባቸው የተገለፁ ሁለት ፈጣን ጀልባዎች እና 60 ሜትር ርዝመት ያለው ጀልባ ማቆሚያ (Jetty) ወደ ሥራ መግባታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

ጀልባዎቹ ፌዴራል ፖሊስ የሕዳሴው ግድብ ላይ ለሚያደርገው ጥበቃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ ከሐይቅ ዳርቻው ወደ ውሃው 60 ሜትር ገባ ብሎ የተሠራው ጀልባ ማቆሚያ እና ጀልባዎቹ በሀገር ውስጥ አቅም የተሠሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

‍‍ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባሕር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎችን በመሠረታዊ ባሕርተኝነት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ከማኅበራዊ ሚዲያ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በፌደራል ፖሊስ የተመደቡ ዘመናዊ የጥበቃ ጀልባዎች በንጋት ሐይቅ ላይ ቅኝት እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በፌደራል ፖሊስ የተመደቡ ዘመናዊ የጥበቃ ጀልባዎች በንጋት ሐይቅ ላይ ቅኝት እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0