ቻድ ሕገ-መንግሥቷን ለማሻሻል እያጤነች መሆኑን አስታወቀች
11:57 06.09.2025 (የተሻሻለ: 12:04 06.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻድ ሕገ-መንግሥቷን ለማሻሻል እያጤነች መሆኑን አስታወቀች
የፓርላማ አባላት በታህሳስ 2023 የወጣውን የቻድ አምስተኛው የሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያዎችን ለመመርመር ልዩ ኮሚሽን እንዲቋቋም አጽድቀዋል።
አንቀጽ 77 የማሻሻያው ዐቢይ ትኩረት ነው፡፡ አንቀጹ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት “ከማንኛውም ሌላ ከተመረጠ የሥራ ቦታ፣ ከማንኛውም የሕዝብ ሥራ፣ እንዲሁም ከማንኛውም ሙያዊ ወይም ትርፋማ እንቅስቃሴ፤ በተጨማሪም ከፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድን ወይም የሠራተኛ ማኅበር ድርጅት ውስጥ ካለ ማንኛውም የሥራ ቦታ” ጋር እንደማይጣጣም ይደነግጋል።
የብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ይህ ድንጋጌ በትርጓሜው ላይ በርካታ ችግሮች ያቀርባል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X