ሩዋንዳ የሰው አልባ በራሪ ታክሲን እውን በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ሆነች

ሰብስክራይብ

ሩዋንዳ የሰው አልባ በራሪ ታክሲን እውን በማድረግ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ሆነች

በኤሌክትሪክ የሚሠራው በራሪ ታክሲ የመጀመሪያ በረራውን በስኬት አጠናቋል፡፡ የፈጠራ ውጤቱ በኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው የ2025 የአፍሪካ አቬዬሽን ጉባዔ ላይ ለዕይታ ቀርቧል፡፡

ይህ ኢኒሼቲቭ መጪውን የአየር ትራንስፖርት ምህዳር በመቅረፅ ረገድ ሩዋንዳ ቁልፍ ሚና እንዲኖራት ያደርጋል ሲል የሀገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ገልጿል፡፡

የመንገደኞች ታክሲ ድሮኑ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር በትብብር መሠራቱ የተገለፀ ሲሆን መሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደ ቻይና እና ብራዚል ባሉ ሀገራት በሥራ ላይ ውለዋል፡፡

ሩዋንዳ ትራንስፖርት ተደራሽ በማይሆንባቸው አካባቢዎች እንደ ደም ያሉ ግብዓቶችን ድሮኖችን ተጠቅማ ራቅ ባሉ ሥፍራዎች በማድረስ በፈር ቀዳጅነት ቀድማ እውቅና ማግኘት ችላለች፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0