የታንዛኒያው የኔሬሬ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የአፍሪካ ትብብር ማሳያ በሚል ተወደሰ
18:36 05.09.2025 (የተሻሻለ: 18:44 05.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የታንዛኒያው የኔሬሬ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የአፍሪካ ትብብር ማሳያ በሚል ተወደሰ
የ2.9 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቱ በአልጀርስ በተካሄደው አራተኛው የ2025 የአፍሪካ የንግድ ትርዒት አድናቆት እንደተቸረው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና እና ቀጣናዊ የፋይናንስ ተቋማት ግዙፍ ራዕዮችን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚችሉ ማሳያ ነው ሲሉ የጉባዔው ተሳታፊ መሪዎችና ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡
ባሳለፈነው ሚያዝያ ወር የጁሊየስ ኔሬሬ የውሃ ኃይል ፕሮጀክት የመጨረሻ ተርባይን ወደ ሥራ መግባቱን ተከትሎ አሁን ላይ 2115 ሜጋ ዋት ኃይል እያመነጨ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ፀሃፊ ዋምኬሌ ሜኔ ፕሮጀክቱን “ጨዋታ ቀያሪ” እና “በነፃ ንግድ ቀጣናው ስር ታላቁ ስኬት” ሲሉ ገልፀውታል፡፡
የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብድልመጂድ ቲቦኔ ፕሮጀክቱ ለቀጣናዊ ትስስር የሚኖረውን ጠቃሚነት በአፅንኦት አንስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X