የሩሲያ የግብርና ዩኒቨርሲቲዎች የሰላ ዕውቀት እና ክህሎት ያላቸው የዘርፉ አመራሮች መውጫ ናቸው - የጋና የፓርላማ አባል

ሰብስክራይብ

የሩሲያ የግብርና ዩኒቨርሲቲዎች የሰላ ዕውቀት እና ክህሎት ያላቸው የዘርፉ አመራሮች መውጫ ናቸው - የጋና የፓርላማ አባል

የጋና ፓርላማ የሥርዓተ-ፆታ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እና የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ዙዋራ ኢብራሂም፤ በሩሲያ 'ኖቮሲቢርስክ ስቴት የግብርና ዩኒቨርሲቲ' የነበራቸውን ጉብኝት አስመልክቶ ሐሳባቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ አካፍለዋል።

"የሩሲያን ግብርና ያራመዱ ቴክኖሎጂዎች እንዴት እንደተዘረጉ ከምንጩ ተመልክቻለሁ። የእኛ የግብርና ሚኒስቴር ሠራተኞች በዚህ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮችን ቢከታተሉ ከዘርፉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች ጋር ስለሚገናኙ የሰላ ክህሎት ይኖራቸዋል። ስለዚህም የትምህርት ዕድልን አስመልክቶ ከዩኒቨርሲቲው እና ከሀገራችን የዘርፉ አመራሮች ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል።

ጋና ለግብርና ተስማሚ የሆነ ሰፊ ለም መሬት ባለቤት መሆኗን ያነሱት የፓርላማ አባሏ፤ ዘርፉን ከባሕላዊ ግብርና ወደ ሜካናይዜሽን ለማሸጋገር የሩሲያ ተሞክሮ እና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

ራስን በምግብ ከመቻል አልፎ የምግብ ምርትን ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ሀገሪቱ የያዘችውን ትልም ለማሳካትም፤ በትምህርት እና ሥልጠና ረገድ ለእርሳቸው ከኖቮሲቢርስክ የተሻለ ተቋም አለመኖሩንም አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0