ማይናማር ለብዝሃ ዓለም ብሩህ ተስፋ የሰነቀውን ብሪክስን በአባልነት መቀላቀል ትፈለጋለች - የገንዘብ ሚኒስትሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱማይናማር ለብዝሃ ዓለም ብሩህ ተስፋ የሰነቀውን ብሪክስን በአባልነት መቀላቀል ትፈለጋለች - የገንዘብ ሚኒስትሩ
ማይናማር ለብዝሃ ዓለም ብሩህ ተስፋ የሰነቀውን ብሪክስን በአባልነት መቀላቀል ትፈለጋለች - የገንዘብ ሚኒስትሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.09.2025
ሰብስክራይብ

ማይናማር ለብዝሃ ዓለም ብሩህ ተስፋ የሰነቀውን ብሪክስን በአባልነት መቀላቀል ትፈለጋለች - የገንዘብ ሚኒስትሩ

የማይናማር የገንዘብ ሚኒስቴር ካን ዛው በምስራቃዊ የኢኮኖሚ ፎረም፤ ‘በደቡብ እና ምስራቅ ዓለም፡ አዲሱን የእድገት ኢኮኖሚ ማን ይመራል?’ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውይይት ላይ ሲናገሩ፤ "ሁላችንም የደቡብ ዓለም ሀገራት ብሪክስን መቀላቀል እንፈልጋለን፡፡ በብሪክስ በኩል፤ ከስብስቡ ጋር በምንፈጥረው ጥምረት አዲስ የእድገት፣ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ምንጮችን ለማግኘት እንፈልጋለን" ብለዋል፡፡

ማይናማር አስቀድማ ለብሪክስ አባልነት ማመልከቷን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ የዩሮኤዥያ የኢኮኖሚ ህብረትን በታዛቢነት ሚና ለመቀላቅል መጠየቋንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ግዜያት ከአንድ ወገን የበላይነት ይልቅ የጋራ አመራር ይፈጠራል፡፡ ብሪክስ፣ የሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና የድቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ህብረት ሚናም በዘላቂነት ያድጋል ሲሉ ካን ዛው ገልፀዋል፡፡

የምዕራባውያን ማዕቀብና የዶላር ፓሊሲ በዓለም ዙሪያ አለመረጋጋትን ፈጥሯል ያሉት ሚኒስተሩ፤ ይህ በተዘዋዋሪ ለሩሲያ፣ ቻይና እና ህንድ የመሪነት መደላደል ፈጥሯል ሲሉ አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የዓለም የነጠላ ስርዓት አብቅቶ ሚዛናዊነት ተተክቷል፡፡ ይህ ለውጥ በ2020 እንደጀመረና የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም የጂኦፖለቲካ ግጭቶች ለዚህ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ብለው እንደሚያምኑ አብራርተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0