ታነዛኒያ ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱታነዛኒያ ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገች
ታነዛኒያ ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.09.2025
ሰብስክራይብ

ታነዛኒያ ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገች

በፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚደገፈው ዘመቻው ዜጎችን በዘላቂ የቆሻሻ አወጋገድ ላይ ለማሳተፍ ያለመ መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዜጎች ቆሻሻን ለይቶ በማሰቀመጥ፣ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል እና የአካባቢ ደህንነት ማስፈን ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ምክር ቤት ተፈጥሮን ለመጠበቅና የጋራ ኃላፊነትን ለማጎልበት በማሰብ የያዛቸው እቅዶች፦

የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ማሳደግ፣

የህብረተሰብ ግንዛቤን ማሳደግ፣

በሰኔ 2026 በየትምህርት ቤቶች ልዩ የአካባቢ ጥበቃ ክበቦችን ማቋቋም፡፡

ታንዛኒያ በየዓመቱ እስከ 20.7 ሚሊዮን ቶን ቆሻሻን የምትሰበስብ ሲሆን ይህም ለውሃ ላይ ሥራዎች መስተጓጎል፣ ለመሠረት ልማቶች ጉዳት እና ለበሽታ ወረርሽኞች ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡

“ይህ ሁኔታ በሀገራችን ያለውን የቆሻሻ አወጋገድ ተግዳሮት ለመቅረፍ የጋራ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ያሳያል” ሲሉ የብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ምክር ቤት የአተገባብርና ማስፈፀሚያ ዳይሬክተር ጀማል ባሩቲ ተናግረዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0