- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የኢትዮጵያ እግርኳስ እና የአፍሪካ ጨዋታዎች መልክ

የኢትዮጵያ እግርኳስ እና የአፍሪካ ጨዋታዎች መልክ
ሰብስክራይብ
''የኢትዮጵያ ህዝብ እግር ኳስ ወዳጅ ነው'' - የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ፡፡
የአፍሪካ ቻምፒዮንሽፕ (ቻን) ጨዋታ ከሰሞኑ ፍጻሜውን ሲያገኝ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያም መካሄዱን ይቅጥላል፡፡
ዛሬ ምሽትም ኢትዮጵያ እና ግብጽ በካይሮ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡
"በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገራት በሊጎቻቸው የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድናቸውን የመወከል ሆነ ራሳቸውን የማሳየት እድላቸው እጅግ የጠበበ ነው'' - የፓን አፍሪካ ፉትቦል ጸሐፊው አሞና ታደለ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቅም ለማሳደግ የውጪ አሰልጣኞች ሚናም ምን ሊሆን ይችላል?
‘‘የውጭ አሰልጣኝ የመምጣት ያለመምጣት አይደለም ጉዳዩ፡፡ መጀመሪያ መስራት ያለብንን ጉዳይ ሳንሰራ የውጭ አሰልጣኝ ብናመጣም ባይታዋር ነው የሚሆነው’’ - የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደሚካኤል፡፡
የአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት፣ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ፣ ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የውጭ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች በኢትዮጵያ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደ ሚካኤል፣ የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ እና የፓን አፍሪካ ፉትቦል ጸሐፊው ኦምና ታደለን በጥልቀት አወያይቷቸዋል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsAfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0