በኢትዮጵያ አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን ለመደገፍ ያለመ ኢኒሼቲቭ ወደሥራ ሊገባ ነው
13:30 05.09.2025 (የተሻሻለ: 13:34 05.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን ለመደገፍ ያለመ ኢኒሼቲቭ ወደሥራ ሊገባ ነው
የተባበሩት መንግሥታት የካፒታል ልማት ፈንድ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ኃላፊ ማይክ ማካፍሪ፤ ከገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመረታ ሰዋሰው ጋር ከሰሞኑ ባደረጉት ውይይት ላይ ይህን እቅድ ማቅረባቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ግዙፍ የግል ኩባንያዎችና ዓለም አቀፍ ባንኮች ለአነስተኛ ንግዶች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ የብድር አቅርቦት ማድረግ እንዲችሉ ልዩ አሠራር ያከተተ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ኢኒሼቲቩ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እድገት ማነቆ የሆነውን የካፒታል በጀት ክፍትት ከዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራር ጋር በማጣመር ለመሙላት ያለመ ነው፡፡
በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ የሥራ ዕድልና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ያግዛልም ተብሏል፡፡
"ይህ ትብብር ንግዶችን ለማብቃት፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመምራትና አካታች የፋይናንስ ዘርፍ ለመፍጠር ያሰቸላል" ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/