ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ትጠብቃለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ትጠብቃለች
ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ትጠብቃለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ትጠብቃለች

ዘርፉ ለኢኮኖሚው አቅም መሆኑ እንዲችል ሁሉንም በማሳተፍ እንደሚሠራ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ሲካሄድ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የ2017 በጀት ዓመት ክንውኖች፦

1.3 ሚሊዮን የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ሀገሪቱን ጎብኝተዋል፣

ከ48 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ጉብኝት አድርገዋል፣

228 ኢንቨስተሮችን ወደ ዘርፉ መሳብ ተችሏል፣

በ “ቪዚት ኢትዮጵያ” የዲጂታል አሠራር የቱሪዝም ሀብት የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል፡፡

ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፦

የሰላም ሁኔታ፣

🪝 የሎጀስቲክስ ጉድለት፣

የሆቴል ደረጃ ምደባ በወቅቱ መረጃ አለመቅረቡ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0