የሩሲያ የአልማዝ አምራች አልሮሳ ከአንጎላ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ዚምባብዌ ፊቱን አዙሯል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የአልማዝ አምራች አልሮሳ ከአንጎላ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ዚምባብዌ ፊቱን አዙሯል
የሩሲያ የአልማዝ አምራች አልሮሳ ከአንጎላ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ዚምባብዌ ፊቱን አዙሯል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.09.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የአልማዝ አምራች አልሮሳ ከአንጎላ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ዚምባብዌ ፊቱን አዙሯል

አልሮሳ በአንጎላው የካቶካ ማዕድን የነበረውን የ41 በመቶ ድርሻ ከሸጠ በኋላ ሥራውን ወደ ዚምባብዌ ማዞሩን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ፓቬል ማሪኒቼቭ  በምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

አልሮሳ እ.ኤ.አ በ2019 በሀገሪቱ ያስጀመረውን የሥነ-ምድር ፍለጋ ስራውን ቀጥሏል ሲሉም ገልፀዋል። ኢንቨስትመንት ማስፋፋት የሚያስችሉ ጥሩ ውጤቶች ይጠበቃሉ ሲሉም አክለዋል።

አልሮሳ አሁን ላይ በአፍሪካ 40 ልዩ ፍቃድ እንዳለው ያነሱት ሥራ አስፈፃሚው፤ ተጨማሪ የአልማዝ እና ሌሎች ማዕድናት ክምችት ለማግኘት እየሠራ ነው ብለዋል።

"ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የረጅም ጊዜ ትብብር አለን። የአልማዝ ፍሰትን ለመቆጣጠር ውጤታማ ስርዓት ለመዘርጋት እገዛ እያደረግን ነው" ሲሉ ማሪኒቼቭ ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0