ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሕር ማዕከል ልትከፍት ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሕር ማዕከል ልትከፍት ነው
ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሕር ማዕከል ልትከፍት ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሕር ማዕከል ልትከፍት ነው

  በግድቡ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ላይ ዘመናዊ የመርከብ አገልግሎቶችን ለመስጠት ሂደት መጀመሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሐይቁን የማልማት ሥራ እየተከናወነ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሥፍራውን የትራንስፖርት፣ የቱሪዝም እና የዓሣ ሀብት ማዕከል ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል።

"አዲሶቹ መርከቦች የመንገደኞች ትራንስፖርት፣ የቱሪስት መዝናኛ እና አሳ ማጥመድን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ይሰጣሉ" ብለዋል አቶ ዓለሙ የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ሲያስረዱ።

በግድቡ አካባቢ ያለውን አነስተኛ አየር ማረፊያ በማሻሻል መደበኛ የበረራ አገልግሎት ማስተናገድ እንዲችል እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0