ለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር
ለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.09.2025
ሰብስክራይብ

ለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር

በ2035 በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረገውን የፋይናንስ ፍሰት ወደ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ለማሳደግ ከቃል ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጠይቀዋል።

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር "አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ድጋፍ ፍትሐዊ ተካፋይ ልትሆን ይገባል" ብለዋል።

"ከፓሪሱ ስምምነት አሥር ዓመታት በኋላ ፍርዱ ግልጽ ነው። ከተቀመጠው ግብ ውጪ ነን። የመጀመሪያው ብይን ይህን አስከፊ እውነታ ያረጋግጣል" ሲሉ ርዕሰ ብሔሩ ተናግረዋል።

አፍሪካ እንደ አህጉር በልማት እና በአየር ንብረት መካከል የማይቻል ምርጫ ሊገጥማት አይገባም ሲሉ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው አህጉሪቱ  በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ የተባበረ ፖሊሲዋን ታስተጋባለች ሲሉ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ለአየር ንብረት ፋይናንስ እንቅፋት የሚሆኑ ቢሮክራሲዎች ሊወገዱ ይገባል - የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0