ባለሃብቶች ከህዳሴው ግድብ እምቅ የዓሣ ሃብት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱባለሃብቶች ከህዳሴው ግድብ እምቅ የዓሣ ሃብት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ
ባለሃብቶች ከህዳሴው ግድብ እምቅ የዓሣ ሃብት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.09.2025
ሰብስክራይብ

ባለሃብቶች ከህዳሴው ግድብ እምቅ የዓሣ ሃብት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

በቀጣይ ቀናት በሚመረቀው የዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ የሚመረተው ዓሣ ባልተደራጀ መልኩ ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታውቋል።

ይህን እምቅ የገበያ አቅም በአግባቡ መጠቀም የሚችሉ ባለሃብቶች እንደሚያስፈልጉም ክልሉ ገልጿል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሐይቁ የዓሣ ምርትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት፦

በ2017 ዓ.ም ዓሣ ለማጥመድ የሚውሉ 55 ጀልባዎች ቀርበዋል፣

በ31 ማህበራት የተደራጁ ወጣቶች ወደ ዓሣ ማስገር ገብተዋል፣

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ በቅርቡ ወደዚህ ሥራ ገብቷል።

በቀን 14 ሺ ኪሎ ግራም ዓሣ የማምረት አቅም ተፈጥሯል።

በ2018 በጀት ዓመት 9 ሺህ 500 ቶን የዓሣ ምርት ከህዳሴው ግድብ ለማግኘት ታቅዷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0