40 የመንግሥት ድርጅቶች በ2017 በጀት ዓመት ከሁለት ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኙ
13:04 04.09.2025 (የተሻሻለ: 13:14 04.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
40 የመንግሥት ድርጅቶች በ2017 በጀት ዓመት ከሁለት ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኙ
ድርጅቶቹን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት የተጣራ 262.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል።
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ88 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ገልጿል።
ለተገኘው ከፍተኛ ገቢ ቀዳሚ ድርሻ ያላቸው ዘርፎች፦
ትራንስፖርት (66.8 በመቶ)፣
የፋይናንስ አገልግሎት (14.95 በመቶ )፣
የቴሌኮምና የኃይል ዘርፍ ( በጋራ 10.08 በመቶ)።
በ2018 በጀት ዓመት 2.75 ትሪሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ እና ከታክስ በፊት 412 ቢሊዮን ብር ትርፍ ለማስመዝገብ ማቀዱን አስታውቋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በ2.5 ቢሊዮን ዶላር የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር መፈራረሙ የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X