በአሜሪካ ሶስት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተገደሉ
12:29 04.09.2025 (የተሻሻለ: 12:34 04.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአሜሪካ ሶስት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተገደሉ
በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት ሲንሰናቲ ከተማ በተፈፀመ የጅምላ ጥቃት እህትማማቾቹ ኤደን አዱኛ (22 ዓመት) እና ፌቨን አዱኛ (20 ዓመት) እንዲሁም በእምነት ደረሰ (27 ዓመት) ህይወታቸውን አጥተዋል።
ጥቃቱን በመፈፀም የተጠረጠረው ግለሰብ ራሱን ለማጥፋት ሙከራ አድርጎ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ከቆየ በኋላ እንደሞተ ፖሊስ አስታውቋል።
ሁለቱ እህትማማቾች ጉድ ሳማሪታን በተሰኘ ሆስፒታል ሲያገለግሉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X