“በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ጠንካራ ትብብር ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ ነው” - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ጠንካራ ትብብር ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ ነው” - ተንታኝ
“በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ጠንካራ ትብብር ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ ነው” - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.09.2025
ሰብስክራይብ

“በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ጠንካራ ትብብር ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ ነው” - ተንታኝ

የቡርኪና ፋሶ የጂኦፖለቲካ ተንታኝ የቭላድሚር ፑቲን የቻይና ጉብኝትን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት "እንዲህ ያሉ ሀገራት ሲተባበሩ እነሱን ማሸነፍ ከባድ ነው" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ቴሄል ሎይ ኮናቴ ይህ ጥምረት "በምዕራቡ ዓለም ፍርሃትን ይፈጥራል" ብለዋል።

"ዛሬ የምዕራባውያንን የበላይነት በመቃወም የተፈጠረው አዲስ ጂኦፖለቲካዊ አሰላለፍ ለአፍሪካ እድልን ያመጣል" ሲሉ አክለዋል።

በዚህ አውድ እንደ ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ያሉ ጥምረቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለብዙ ሀገራት ሳቢ እየሆኑ መጥተዋል ብለዋል።

"የሻንጋይ ትብብር ድርጅት የጂኦፖለቲካዊ አቋም አስገዳጅ ያልሆነ እና ሀገራት አሰላለፉን ካልተቀላቀላችሁ በጠላትነት ትታወጃላቹ ብሎ የማያስገድድ ሳቢ ራዕይ ነው" ሲሉ ኮናቴ ገልፀዋል።

ስለዚህ በድርጅቱ እና ብሪክስ ሀገራት “የአሜሪካን የበላይነት ሚዛናዊ የማድረግ ሂደት ውስጥ”፤ አፍሪካ “የጂኦፖለቲካዊ አስተዋፆኦዋን በአዲስ መሠረት መገንባት ትችላለች” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0